የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይሬክቶሬት በዩኒቨርሲቲዉ የተከናወኑ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ለህይታ አቀረበዶ/ር ሀይማኖት የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ

ዝግጅቱ የተከሄደዉ ሚያዚያ 30/2009 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሠራተኞች በተገኙበት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ሲሆን ዓላማዉም በዘርፉ ሲከናወን የነበረዉን የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ለማበረታታት ብሎም በዩኒቨርሲቲዉ የሚኒ ሚዲያና ኪነ ጥበብ አባላት አማካኝነት የተሰራዉን ‘ዘፀሐት’ የተሰኘ ቲያትር ለማስመረቅ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡
ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት የዩኒቨርሲቲዉ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ  እንደተናገሩት መድረኩ እጅግ ጠቃሚ፣ የመማማሪያና መመካከሪያ እንደሆነ በመግለጽ የተዘጋጀዉ ፕሮግራም እስኪጠናቀቅ ድረስ በጥሞና እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡

የኪነ ጥበብ ሥራዎች በክፊል
በፕሮግራሙ ላይ የቀረቡት የኪነ ጥበብ ዉጤቶች ዉስጥ ስለ አሶሳ ዩኒቨርሲቲና አከባቢዉ የሚገልጽ መዝሙር በመምህር ፍቅረስለሴ ተደርሰዉ ቀርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መሳጭ እና ጥልቅ ትርጉም ያዘለ ስለ ሀገርና ስደት የሚያትት ግጥም እንዲሁም ድንቅ ትወና የታየበት መነባነብና በተማሪ ናታንም አያለዉ ተደርሰዉ ለህይታ የበቃዉ ዘፀሀት ቲያትር ለዝግጅቱ ድምቀት ሆኖ አምሽተዋል፡፡ የትያትሩ ይዘትም ከአስከፊዉ የ1977 ዓ/ም ረሀብ ከዚያም ጋር ተያይዞ የነበረዉን ስደት እና ጦርኔት ጀምሮ እስከ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ያለዉን የዜጎቿን ተሳትፎ የሚያሳይ እንደነበረ ተስተዉሏል፡፡

 
የቲያትሩ ተሳታፊዎች በክፊል

 

Who's Online

We have 5 guests and no members online

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በአሶሳ ኤፍ.ኤም 88.3 የፕሮግራም ስርጭት ጀመረ
 
ዩኒቨርሲቲያችን የሚያከናውናቸውን የመማር ማስተማር ፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ከአሶሳ ኤፍ.ኤም 88.3 ጋር ውለታ በመግባት እየሰራ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 12፡1ዐ ሰዓት ጀምሮ ለ2ዐ ደቂቃ ያህል 

የስራ እንቅስቃሴውን በአየር ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ስለዚህ የተከበራችሁ አድማጮቻችን በፕሮግራሙ ላይ ያላችሁን አስተያዬት በስልክ ቁጥር 0577750784 ወይም በህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ቢሮ በአካል በመቅረብ በመስጠት ለፕሮግራማችን መሻሻል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ


Copyright © 2016. All Rights Reserved.