Assosa University

ዩኒቨርሲቲው በመተግበር ላይ በሚገኘው አዲሱ ተቋማዊ መዋቅር  መሰረት ምደባ ከተሰጣቸው አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲሱን ተቋማዊ መዋቅር  በመተግበር ላይ  የሚገኝ ሲሆን በመዋቅሩ መሰረት ቡድን መሪና ከዚያ በላይ መደቦች ላይ  ከተመደቡ አመራሮች ጋር  ስለተቋሙ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ በዛሬው እለት ውይይት አካሄዷል።

በዉይይቱ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ስለ አዲሱ ተቋማዊ አደረጃጀት እና  ዓላማው ማብራሪያ ሰጠዋል።

በአዲሱ መዋቅር የዩኒቨርሲቲው የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ኃላፊ ሆነው የተመደቡት አቶ አዲሱ አዳሜ የዩኒቨርስቲውን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስመልከት ሰነድ አቅርበዋል።

በውይይቱ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንቶች የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕረዝዳንት  የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው አለሙ ውይይቱን በጋራ መርተውታል።

(ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም)

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት/ Assosa University Public and International Relations Directorate

Face book: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/assosauniversity_official

Website: https://www.asu.edu.et

Email: pir@asu.edu.et

PoBox 18

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *