Assosa University

የነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ የተከናወኑ የጥናት ውጤቶች ማረጋገጫ የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሄደ 

(መጋቢት 21/2015 ዓ/ም) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ ለአቅመ  ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች ለሴቶችና ህፃናት እንድሁም ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በአሶሳ ከተማ፣ በባምባሲ እና በግልገል በለስ ከተማ ሶስት ማዕከላትን በመክፈት ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሥራዎችን በመስጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

 ከዚህ ጋር ተያይዞም የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ  የሕግ  ት/ቤት  ከልማት ለሁሉም ማህበር እና ከካናዳ ኢምባሲ ጋር በመተባበር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመሰጠት  ላይ የሚገኘውን የነፃ የሕግ ድጋፍ አሰጣጥ አስመልክቶ የተከናወኑ የጥናት ውጤቶች ማረጋገጫ የምክክር መድረክ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ  የቤ/ጉ/ ክልል  የነፃ የሕግ ድጋፍ አሰጣጥን አስመልክቶ የተከናወኑ የጥናታዊ ጽሁፍ ግኝቶችን ለመገምገም እና የነፃ የሕግ ድጋፍ ከሚሰጡ ተቋማት ጋር የጋራ ጥምረት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ለማካሄድ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ዩኒቨርስቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት  ዶ/ር አብዱልሙስን ሀሰን በፕሮግራሙ መክፈቻ ወቅት ገልፀዋል።

በመድረኩም አንድ የምርምር ጽሁፍ እና የውይይት መነሻ ሰነድ በዩኒቨርስቲው የህግ መምህራን ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል። በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው  የምር/ማህ/አገ/ም/ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልሙስን ሀሰን በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ወቅት እንደተናገሩት ነፃ የሕግ ድጋፍ  አገልግሎት ፕሮግራምን በክልሉ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ኃላፊነት በመወጣት የፍትህ ተደራሽነቱን ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *