Assosa University

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገር ወዳድ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ክበብ አስተባባሪዎች ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጡ

(መጋቢት19/2015 ዓ.ም)

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገር ወዳድ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ክበብ በ2014 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን የተመሰረተበት ዓላማም፡- ተቋማዊ ልህቀት እና የተማሪዎች ስኬት ባህል በመፍጠር የዩኒቨርሲቲውን የተልዕኮ ስኬት ለማገዝ የተቋቋመ ክበብ ነው፡፡

ከዚህም አላማ ጋር ተያይዞ ክበቡ ለ400 ተማሪዎች ከመጋቢት 14-19 /2015 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የሥልጠናው አስፈላጊነትም የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ በመጨመር ዉጤታቸውን ለማሻሻል፣ የተማሪዎቹን ባህሪ ለማነፅና መገንባት እንድኁም እንደሀገር የጥገኝነት፣ የነፃነትና የመደጋገፍ መርሆዎችን መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ለማስረጽ ታስቦ የተሰጠ ሥልጠና መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር አበራ በይሳ በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ገልፀዋል፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

telegram: https://t.me/assosauniversity_official

website: https://www.asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *