Assosa University

የዩኒቨርሲቲው የስድስት ወር በጀት አፈጻጸም መልካም ውጤት የታየበት መሆኑ ተገለጸ

የዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም በዩኒቨርሲቲው ካውንስል መገምገሙ የሚታወስ ስሆን በዩኒቨርሲቲው ልከናወኑ ከታሰቡ ሥራዎች አንጻር የመደበኛ እና የካፕታል በጀት አስተዳደር የስድስት ወር አፈጻጸም መልካም ደረጃ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁም መሠረት ዩኒቨርሲቲው የ2016 የግማሽ ዓመት (የስድስት ወር) የበጀትና ፋይናንስ አስተዳደር አፈጻጻሙን የመንግስ ፋይናንስ አዋጅ በአስቀመጠው አግባብ ለህዝብ ግልጽ ያደርጋል።

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ግልጽ፣ ውጤታማ እና የጸዳ የበጀት አስተዳደር ማረጋገጥ በመቻሉ እንዲሁም የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በጊዜ ማቅረብ በመቻሉ ከገንዘብ ሚኒስቴር የእውቅናና የምስክር ወረቀት የተበረከተለት መሆኑም ይታወሳል።

(ጥር 25/05/2016 ዓ.ም)
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ / Assosa University Public and International Relations Executive
Face book: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/assosauniversity_official
Website: https://www.asu.edu.et
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *