የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እጦት ምክኒያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በቡልድግሉ ወረዳ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለሚገኙና መማር ላልቻሉ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያግዛቸው ከዚህ በፊት ቃል በተገባው መሰረት 3000 ደብተርና 1000 እስክብርቶ ድጋፍ አደረገ። የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉንም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱረሂም ለአሶሳ ዞን ም/አስተዳዳሪ እና ለብልድግሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በተገኙበት አስረክበዋል።