logo

ማስታወቂያ፤ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

Posted On: March 25, 2020

የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰዓት የዓለም ስጋት በመሆኑ የሚኒስትሮች ምክርቤት መጋቢት 15/2012 ዓ/ም ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ ያስተላለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማኔጀመንት በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ በመወያየት ከቀን 16/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ወሳኔዎችን እሰተላልፏል፡፡ 1. ሁሉም የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ወደ መጡበት አካባቢ በመመለስ ራሳቸዉን ከከኮቭዲ 19 በሽታ እንዲከላከሉ 2. ከክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የህዝብ መጓጓዣ መኪናዎችን ማመቻቸት 3. የሁሉም ኮሌጆች መምህራን በቤታቸዉ ሆነዉ እብዲሰሩ 4. የዩኒቨርሲቲዉ የአስተዳደር ሰራተኞች ከተወሰኑ የስራ ክፍሎች ሰራተኞች በስተቀር ከቤታቸዉ በመሆን የራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉ እንዲከባከቡ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

Image

ማስታወቂያ :-ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

Posted On: March 19, 2020

የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰዓት የአለም ስጋት መሆኑ በብዙሀን መገናኛዎች እየተሰራጨ ይገኛል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገድ በሰዎች ንክኪ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ሰዎች በብዛት የሚገኙበት ቦታ እንደመሆናቸው መጠን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የበሽታዉ ስጋት እስኪቆም ድረስ በዩኒቨርሲቲዉ ሊወሰዱ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ በቀን 07/07/2012 ዓ.ም በመወያየት የሚከተሉትን ውሳኔዎች በማስተላለፍ ከ08/07/2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

 1. በዩኒቨርሲቲው ሰባት አባላት ያሉት ግብረ ኃይል አቋቁሞ የበሽታዉን ሁኔታ በየቀኑ እየተከታተለ እና መረጃ እያደራጀ ለህዝብ ተደራሽ ያደርጋል፡፡
 2. ከ08-07-2012 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት መምህራን ለተማሪዎች ፊት ለፊት የሚያሰተምሯቸዉን ትምህርቶች በማሰቀረት ለተማሪዎች Hand out, reference books, and soft copy materials በበቂ ሁኔታ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም በግላቸዉ/ በዶርማቸዉ ሆነዉ እንዲያነቡ፤ መምህራን በኢሜይልና በተለያዩ ዘዴዎች የመማር ማስተማሩን ስራ አንዲመሩት የተወሰነ ሲሆን፤ ይህንን ተግባራዊ ማድረጋቸዉን በኮሚቴው ይረጋገጣል፡፡
 3. ተማሪዎች በምግብ ቤትና ቤተ-መፅሀፈት አካባቢ መተፋፈግን ለማስቀረት የመቀመጫዎች መጠጋጋት እንዳይኖር የአገልግሎት ሰዓት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
 4. በዩኒቨርሲቲው ስብሰባዎች እንዳይኖሩ፤ አስገዳጅ ስብሰባዎች እንኳ ቢኖሩ ሰፋ ባለአዳራሽ አንዲካሄዱ፡፡
 5. በዩኒቨርሲቲው 11/07/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ታስቦ የነበረው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረስ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
 6. የተለየ የበሽታዉ ምልክት ቢከሰት የተጠርጣሪዎች ለይቶ የማቆያ ክፍል እና የጥቆማ ለመስጠት ስልክ ቁጥር (0917072312) ይጠቀሙ፡፡
 7. ለበሽታ ቅድመ መከላከል የሚውሉ የንጽህና መጠበቂያና አስፈላጊ ቁሳቁሶች ለተማሪዎችና ለበሽታው ተጋላጭ ሠራተኞች በነፍስ ወከፍ እንዲሰራጩ፤ በማዕከላትም እንዲቀመጡ መወሰኑ፡፡
 8. ከክልሉ ጋር በመሆን COVID_19 የመከላከል ሥራ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑ፡፡
 9. ለተቋሙ ሠራተኞች የሚያገለግሉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች በወንበራቸው ቁጥር ብቻ እንዲጭኑ የሚሉት ነጥቦች የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ወስኖ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ

Image

ማስታወቂያ

Posted On: March 17, 2020

ለሁሉም የአሶሳ ዩኒቨረሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰዓት የአለም ስጋት መሆኑ በብዙሀን መገናኛዎች እየተሰራጨ ይገኛል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መሰራጫ መንገድ በሰዎች ንክክ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲ ሰዎች በብዛት የሚገኙበት ቦታ በመሆኑ  የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የበሽታዉ ሁኔታ እስክረጋጋ ድረስ በዩኒቨርሲቲዉ ሊወሰዱ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ በመወያየት የሚከተሉትን ወሳኔዎች አስተላልፏል፡-

 • 7 አባላት ያሉት ግብረ ኃይል አቋቁሞ የበሽታዉን ሁኔታ በየቀኑ እየተከታተለ እና መረጃ እያደራጀ  የተቋሙን ሁኔታ ለህዝብ ተደራሽ ያደረጋል
 • ከ08-07-2012 ዓ/ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ት/ት እንዳይናር ተደረጓል
 • ከ08-07-2012 ዓ/ም ጀምሮ መምህራን ለተማሪዎች ፊት ለፊት የሚያሰተምሯቸዉን ት/ቶች በማሰቀረት ለተማሪዎች Hand out, reference books,online and soft copy materials በበቂ ደረጃ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም የበግላቸዉ/ በክፍላቸዉ ሆነዉ እንዲያነቡ፤ መምህራን በኢሜይልና በተለያዩ ዘዴዎች የመማር ማስተማሩን ስራ አንዲመሩት የተወሰነ ሲሆን፤ ይህንን ተግባራዊ ማድረጋቸዉን አንዲረጋገጥ
 • ተማሪዎች በምግቤትና ላይበራሪ አካባቢ መተፈፈግን ለማስቀረት የመቀመጫዎች ጥግግት እንዳይኖር የአገልግሎት ሰዓት ማራዘም
 • አስገዳጅ ስብሰባዎች እንኳ ቢኖሩ ሰፋ ባለአዳራሽ አንዲካሄዱ
 • የተለየ የበሽታዉ ምልክት ቢከሰት የተጠርጣሪዉ ማቆያ ተለይቷል

Image

Call for Papers for International Research Conference on “One Health in Ethiopia”

Posted On: March 07, 2020

International Research Conference on “One Health in Ethiopia”

Image