Assosa University

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማርች 8 የሴቶች ቀንን በደማቅ ሁኔታ እያከበረ ነው

በዛሬዉ እለት በዩኒቨርሲቲዉ እተከበረ ያለዉ በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ ፣ በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ ተከብሮ ያለፈ ሲሆን በዩኒቨርሲቲያችን ደረጃ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ታጂቦ በመከበር ላይ ነዉ።
በበአሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር አብዱል ሙህሴን ሀሰን የበአሉን አከባበር ዓላማ ሲናገሩ በአሉን ሰናከብር የሴት መምህራን፣ሰራተኞች እና ተማሪዎች ችግር ላይ ተወያተን መፍትሄ ለማሰቀመጥ እና ሴቶች ለመብታቸው በቂ ግንዛቤ ኖሯቸዉ የሚደርስባቸዉን ጭቆናና የመብት ጥሰት የሚያወግዙበት፣አንድነታቸዉን በማጠናከር ድምጻቸዉን በጋራ የሚያሰሙበት እንዲሁም ልምድ የሚለዋወጡበትና ለበለጠ ትግል ተቀናጅተዉ ለመንቀሳቀስ ቃል የሚገቡበት ቀን መሆኑን ለማስገንዘብ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባዋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በበአሉ አከባበር ላይ የሴቶችን ልእልና ከፍ የሚያደርጉ ስነፅሁፎችና መነባንቦች የቀረቡ ሲሆን በበአሉ ላይም የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ሰራተኞች፣መምህራን፣ተማሪዎችና ከክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዉ አክብረዋል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *