Assosa University

ለዩኒቨርሲቲው የግቢ ፓሊስ ሠራተኞች መሰረታዊ የተቋም ደህንነት ፍተሻ ሥልጠና ተሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በግቢ ጥበቃና ደህንነት ሥራ ክፍል ለሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የግቢ ፓሊስ ሠራተኞች ከህዳር 13/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት መሰረታዊ የተቋም ደህንነት ፍተሻ፣ ፈንጂና የሚፈነዱ ነገሮችን መለየትና የጥንቃቄ እርምጃዎች እና የቀውስ ጊዜ አስተዳደር ህጎችና የግቢ ፓሊስ ሰራተኞች ተግባርና ኃላፊነትን በሚመለከቱ ይዘቶች ከኢትዮጲያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኞች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥራ አመራር ተቋም ሥልጠና ተሰጥቶል። የሥልጠናው አላማም፡- ለግቢ ደህንነት ሠራተኞች ቀጣይነት ያለው የስራ ላይ ሥልጠና በመስጠት ዩኒቨርሲቲውን ምቹ የሥራ አካባቢ በማድረግ የተሻለ የግቢ ጥበቃ አገልግሎት ለማገኘት ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መልካሙ ደሬሳ በሥልጠናው መክፈቻ ወቅት ገልፀዋል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ ወቅት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው አለሙ በሥልጠናው መክፈቻ ወቅት በእውቀት፣በክህሎት እና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፁ ተማሪዎች እንድናፈ የግቢ ፓሊስ ሠራተኞች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑንአውስተው በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተዘጋጀውን ሥልጠና መውሰዳችሁ ዩኒቨርሲቲው በሚሊዮን ወጭ አድርጎ የተከላቸውን ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ ለመጠቀምና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ግብዓት እንደሚሆናቸው ለስልጠናው ተሳታፊዎች መልዕክት አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *