(ጥር 27/2017 ዓ/ም) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ከባለ- ድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አድርጓል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ ዩኒቨርሲቲዉ ከመማር ማስተማር በተጓዳኝ በርካታ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ዶ/ር ከማል አክለዉም ዩኒቨርሲቲዉ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና ትብብር የሚሰሩ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል የአካባቢዉን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በመርሃ ግብሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል፡፡
የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የስትራቴጂ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታከለ መኮንን በዩኒቨርሲቲዉ የተከናወኑ አበይት ተግባራት አፈፃፀም፣ የታዩ ጥንካሬና ድክመቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተቀመጡ የመፍትሔ ሀሳቦች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ማመብራያ ሰጥተዋል።
በተያያዘም የቀረበውን ሪፖርት መሰረት ያደረገ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን ክልሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት መገኛ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዉ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት የአካባቢዉን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ከባለ ድርሻ አካላት የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችን እንደግብአት በመዉሰድ በዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች የማብራሪያ ሀሳብ ተሰጥቶበት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#