ካዉንስሉ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በአራቱም ዘርፎች በፕሬዚዳንት፣በአካዳሚክ፣በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአስተዳደር እና ልማት ከእቅድ አኳያ የተከናወኑ ዉጤቶች በስትራቴጂ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ታከለ መኮንን ቀርቦ የግምገማ ዉይይት ተካሂዶበታል።
በሪፖርቱ በግማሽ አመቱ ዉጤታማ የሆነ የመማር ማስተማር ስራ መሠራቱ እና በማህበረሰብ አገልግሎቱ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ አበረታች ሥራዎች መሠራታቸዉ ሊቀጥሉ የሚገቡ ዉጤታማ ሥራዎች መሆናቸዉ ተመላክቷል።
በተጨማሪም በሪፖርቱ መካተት ያለባቸዉ እና መስተካከል ይኖርባቸዋል የተባሉ ሀሳቦች በካዉንስሉ አባላት ከተነሱ በኋላ የየዘርፍ ሀላፊዎችም በተነሱት ነጥቦች ማብራሪያ እና ምላሽ ሠጥተዉባቸዋል።
በሌላ መልኩ በሪፖርት ግምገማዉ መሻሻል ይገባቸዋል ተብለዉ ከተነሱት ሥራዎቻችን የትኩረት መስክ ልየታን መሠረት አድርጎ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸዉ፣የግዥ አገልግሎት በኤሌክትሮኒክ ሲስተም መሆኑ መልካም ጅምር ቢሆንም በዕቅዱ መሠረት ግዥ መፈጸም ቢቻል እና የትራንስፖርቱ አገልግሎት ማሻሻል ትኩረት ተሠጥቷቸዉ መሠራት እንደነበረባቸዉ እና በቀጣይ ሁለተኛዉ ግማሽ ዓመትም አፈጻጸማቸዉ ሊሻሻል ይገባቸዋል ተብለዉ ከተነሱት ነጥቦች መካከል ናቸዉ።
የግምገማ ዉይይቱን የመሩት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም እንደተቋም በቀጣይ አፈጻጸማቸው መሻሻል የሚገባቸዉ ሥራዎችእንዳሉ ሆኖ በዚህ ግማሽ ዓመት ያስመዘገብናቸዉ ዉጤቶች ልናሳንሳቸዉ የሚገባ አይደለም ብለዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#