በአካዳሚክ በሀላፊነት መደቦች ላይ የመጀመሪያ መስፈርትን ያሟሉ ተወዳዳሪዎች ስትራቴጂክ እቅዳቸዉን አቀረቡ በአካዳሚክ አመራር ቦታዎች ምልመላና ምደባ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት አዲስና ነባር የስራ መደቦች ላይ መምህራንን በማወዳደር ለመመደብ ማስታወቂያ በወጣባቸዉ የምህንድስና ኮሌጅ ዲን እና ኤሌይክትሮኒክ ትምህርት ዳይሬክተር መደቦች ላይ የተወዳደሩ አመልካቾች የስትራቴጂክ እቅዳቸውን ዛሬ አቅርበዋል።የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ጨምሮ፤ ምክትል ፕሬዝዳንቶች የኮሌጅ ዲኖች፣ዳይሬክተሮችና የሚመልከታቸዉ የትምህርት ክፍል ሃላፊዎች የውድድሩን ሂደት በመታደምና ድምጽ በመስጠት ተሳትፈዋል ። ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉንTwitter:Assosa University (@AssosaU) / XWhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21PFacebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficialTelegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2NkEmail: pir@asu.edu.etInstagram: https://www.instagram.com/asueduet/#