በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገር በቀል እዉቀት ጥናት ኦፊሰር አስተባባሪነት ለቲያትርና ሥነ-ጹህፍ አባላት ለሦስት ቀናት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ፡፡
በሥልጠናዉ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሀገር በቀል እውቀት ጥናት ኦፊሰር ዶ/ር አልማዝ ደቼ ሲሆኑ ተቋሙ የአሶሳ እና አካባቢው ባህል እና ትውፊት እንዲጠና፣ እንዲሰነድና ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ኪነ ጥበብ ዓይነተኛ ሚና ስላለው ማዕከሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር አልማዝ አክለዉም የማዕከሉ አባላትና የኪነ ጥበብ ማህበራት ያላቸውን መክሊትና ተሰጥኦ በአግባቡ በመጠቀም ባህልንና ሀገር በቀል ዕዉቀንት አፍቃሪ፣ ጠባቂና ተንከባካቢ ትዉልድ ለመፍጠር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናዉ በአቶ ታከለ መኮንን እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በስልጠናው የዩኒቨርሪቲዉ የቲያትርና ሥነ-ጹህፍ አባላት፣ የአሶሳ ህዳሴ ኪነ- ጥበብ ማህበር አባላት እና የገመሀሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የባህል ማዕከል ኪነ-ጥበብ ተጠሪና አባላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
ስልጠናዉ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በቱፊታዊ ተዉኔት እና ሥነ-ጹህፍ በማህበረሰቡ ያለዉ አመለካከትና ለሀገር ዕድገት ያለዉ ፋይዳ ዙሪያ እንደሚቀጥል ተገልጧል
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#