አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ስመዘገቡ ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ22/11/ዐ9 ዓ.ም በ2ዐዐ9 የበጀት ዓመት ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የት/ት ክፍል ሀላፊዎች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና መካከለኛ አመራሮች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡

ያንብቡት…

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ት/ት በመስጠት ላይይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀምሌ ወር 2ዐዐ8 ዓ.ም በሶስቱም ዞኖች ለተውጣጡ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ከክልል ት/ት ቢሮ ጋር በመሆን ምልመላውን ካደረገ በ|ላ ትምህርቱን በመስጠት ነበር ይህን የክረምት የመጠናከሪያ ፕሮግራም የጀመረው፡፡

ያንብቡት…

FH ኢትዮጵያ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉገለፀ

ሀምሌ 29/2ዐዐ9 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህራን፣ የአልሙናይ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የፋርም ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ FH ኢትዮጵያ በሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የቁጥብ እርሻ ልማትን ተገባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

ያንብቡት…

The Universiyty Provides Deliverology Training for all Level Leaders
The Universiyty provided one day training for the presidents, College Deans , directors ,coordinators and department heads on August 15/2009 E.C. The objective of the training was to introduce the new concept of deliverology, higher education targets on deliverology as well as what is planning in deliverology and how it implements.
read more...

Assosa University’s Bamboo seedling plantation

The month of August is the commemorating month of the late Prime Minister Meles Zenawi death in the country level.
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡የምርምርና  ማህበረሰብ  አገልግሎት  ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሃይማኖት ዲሳሳ በ መርሃ- ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት  ዩኒቨርሲቲያችን ባዘጋጀዉ  የመግባቢያ ሰነድ  በጋራ ለመስራት  ጥሪ የተደረገላችሁ  የክልል ሴክተር  መስሪያቤት  ሃላፊዎች  በቅድሚያ ጥሪያችን  አክብራችሁ  እዚህ  በመገኘታችሁ  በዩኒቨርሲቲዉ  ስም  ከፍያለ  ምስጋናየን  እያቀረብኩ  በዛሬዉ ዕለት የምናደርገዉ  የዉል ስምምነት ማለት  የገንዘብ  እርዳታ  ሳይሆን  እዉቀትንና  ሃብትን በማቀናጀት  የጋራ  በሆኑ  እቅዶች ላይ  ተመስርቶ  የመስራት  ባህልን  ለማዳበር  ወሳኝ  ሚና  አለዉ ሲሉ  ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ

ትስስሩን ለመፈጠር የታለመበት ዋና  ዓላማ ዩኒቨርሲቲዉ ከክልል ሴክተር  መስሪያ ቤቶች ጋር በትምህርት እና ስልጠና፣በስራ እድል ፈጠራ፣በቴክኖሎጅ ሽግግር እና በምርምር ተደጋግፎ ለመስራት ታስቦ የተደረገ የዉል ስምምነት ነዉ፡፡በዉል ስምምነቱ ከታቀፉት መስሪያ ቤቶች  ለምሳሌ ያክል  የቤ/ጉ/ክ/መ/ ክልል ምክርቤት ፣የቤ/ጉ/ክ/መ/ ፍትህ ቢሮ፣የኢ/ያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት አሶሳ ሪጅን፣ የቤ/ጉ/ክ/መ/ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የቤ/ጉ/ክ/መ/ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ሃብት ቢሮ ይገኙበታል፡፡የሚፈጠረዉን ትስስርም  በማበረታት፣ ዘርፉን  በላቀ ሁኔታ በመምራት ፣በማስተባበር፣ በመከታተልና  በመደገፍ  ሃገራዊ  ተልዕኮዉን  በብቃት  እንዲወጡ  የእንዱስትሪ  ትስስር  ዳይሬክቶሬት  ዳሬክተር  መ/ር ከፊያለው  አስረድቷል፡፡

መ/ር ከፍያለዉ ገለታ የትስስሩን ዓላማ ሲያስረዱ

ከተሳታፊዎች የተሰጠ  አስተያየት  ይህ የመግባቢያ  ሰነድ ተዘጋጅቶ  መቅረቡ  ለዩኒቨርሲቲዉም ሆነ  ለክልሉ ሴክተር  መስሪያቤቶች  የሚሰጠዉ  አስተዋፅኦ  የጎላ መሆኑን  ገልፀው  በ2010ዓ.ም የበጀትዓመቱ ዕቅድ ላይ አካተን  በማቀድ  ተግባራዊ ማድረግ  ያጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ተሳታፊዎች በሰነዱ ላይ አስተያዬታቸዉን ሲሰጡ
የዉል ስምምነት ሰነድ የፊርማ ሥነ ስርዓት ሲካሄድ


Copyright © 2016. All Rights Reserved.